Watch Eyuna emenu sewoch “እዩና እመኑ ሰዎች” Best Ethiopian orthodox Mezmur -Yilma Hailu on WongelTube Ethiopian Orthodox Tewahido Website
ቅድመ ልደተ ክርስቶስ 1000 ዓመት አስቀድሞ በሐልዎተ እግዚአብሔር የነበረውን ኋላም በዘመነ-ሐዲስ ከእስራኤል ቀጥሎ ክርስትናን በመቀበል መፅሐፍ ቅዱስን በራሱ ቋንቋ ተርጉሞ ለ2000 ዓመታት ያህል ወንጌልን ሲማርና ሲሰብክ እግዚአብሔርን ሲያመልክና ሲያስመልክ የኖረውን ፍጹም እምነት ያለው ክርስቲያን ደርሶ ወንጌል እንስበክባላችሁ ጌታን አልተቀበላችሁም ማለት‹‹ ለቀባሪው አረዱት›› እንደማለት ነው፡፡ በቤ/ክ ከጌታ ስም ይልቅ የቅዱሳን ስም ገኖ የሚጠራ ቤ/ክ በወንጌል ሳይሆን በባህል የምትመራ የሚመስላቸው የዋሃን ጥቂቶች አይደሉም፡ ቤ/ክ በገድሉ፤ በድርሳኑ ፤በመልካ መልኩ፤ በድጓው፤ በመፅሐፍቶቿ፤ በቅዳሴዋ፤ በማኅሌቷ ፤በሰዓታቷ በሁሉ ነገሯ ክርስቶስን ትሰብካለች፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰው ውዳሴ ማሪያም 63 በመቶ የሚናገረው ስለ ክርስቶስ መሆኑን ስንቶቻችን አናውቃለን? ትልቅ ነገር የተናገሩ ይመስል ‹‹ኢየሱስ ጌታ ነው! ››ብለው ጆሮአችን እስኪበጠስ ድረስ እንደ ብራቅ የሚጮሁብን ፕሮቴስታንቶች ቤ/ክ ክርስቶስን ‹‹የጌቶች ጌታ፤ የነገስታት ንጉስ፤ የአማልክት አምላክ›› ብላ ባሏት ሃብቶች ሁሉ እንደምታወደሰው ያውቁት ይሆን? ኢየሱስ የሚውለን ስም በስምንተኛው ቀን ያወጣችለትን ድንግል ማርያምን ብናከብር እርሱንና ስሙን አላከበርንም ትላላችሁ?
አዳዲስ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች እና ስብከቶችን ይመልከቱ:: ለጉዋደኞችዎም በማካፈል ሃይማኖትዎን ያስፋፉ: ያጠንክሩ: ወንጌልቲዩብ የተዋህዶ መዝሙር ድረ-ገጽ
Watch Latest Ethiopian Orthodox Mezmure and Sibket Videos – Share this video with your friends to spread the word of God and strength Ethiopian Orthodox Tewahido.
Like WongelTube on Facebook. Don’t Miss the new Mezmur.