Watch +++ገብርኤል Gebriel +++Ethiopian Orthodox mezmur about Kidus Gabriel 2 on WongelTube Ethiopian Orthodox Tewahido Website
ገብርኤል ማን ነው?
ገብርኤል ማለት “ እግዚእ ወገብር” – የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው። ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበት በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወራቸው መላእክትም “ መኑ ፈጠረነ፡ ማን ፈጠረን ” ሲሉ ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹ ጊዜ “ የፈጠረንን አምላካችን እስክናውቅ በያለንበት ጸንተን እንቁም ” ብሎ ያረጋጋቸው መልአክ ነው። በዚህም ምክንያት ጌታ “ በእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም ” እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል። ከዚህም በኋላ ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል።ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ በክርስቲያኖች ዘንድ ይወደዳል፡፡ ምክንያቱም ያዘኑትን ለማጽናናት የምሥራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ይላካልና፡፡
*ይህ ቅዱስ ገብርኤል ነው*
ሰጥናኤል ሥላሴን በካደ ጊዜ መላእክትን በቃሉ ያጽናናቸው
*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም
*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ ይህ
*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡*
የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ
*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡*
ዳንኤልን ከአናብስት ያዳነው
*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነቸው
*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ወደ ዘካርያስ የተላከ የዮሐንስን ልደት ያበሰረ
*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ
*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡*
ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው
*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ሰብአ ሰገልን በኮከብ ምልክት የመራቸው
*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ድንግል ማርያምና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ
* ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
የብርሃን ራስ ወርቅ የተቀዳጀ
*ገብርኤል ነው፡፡*
የአሸናፊና የኃይል መልአክ
*ገብርኤል ነው፡፡*
ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ
*ገብርኤል ነው፡፡
በቅዱስ ገብርኤል ብስራት፥ ምልጃ ፥ ተራዳኢነት እና ፈጥኖ ደራሽነት የማይሆን የለም:: እግዚአብሔር የወደደው ፥ አረጋጊና አብሳሪ መልአክ የሆነው የቅዱስ ገብርኤል ረድኤት እና ምልጃ ከሁላችን ጋር ይሁን! በያለንበት ከለላ ይሁነን። መልካም በዓል ይሁንልን አሜን አሜን!
Song ሰላምን እተውላችኋለሁ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ
እኔ የምሰጣችሁ አለም እንደሚሰጠው አይደለም
ልባቹ አይደንግጥ አትፍሩም ዮሐ 14:27
የቻነላችን አባል መሆንዎትን እንዳይዘነጉ [Please subscribe to our YouTube Channel here]: https://www.youtube.com/keraniyo
Ethiopian Orthodox Mezmur Tewahedo collection
Christian life and faith.
በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፥19). በማህበረ ቅዱሳን የተዘጋጀ
አዳዲስ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች እና ስብከቶችን ይመልከቱ:: ለጉዋደኞችዎም በማካፈል ሃይማኖትዎን ያስፋፉ: ያጠንክሩ: ወንጌልቲዩብ የተዋህዶ መዝሙር ድረ-ገጽ
Watch Latest Ethiopian Orthodox Mezmure and Sibket Videos – Share this video with your friends to spread the word of God and strength Ethiopian Orthodox Tewahido.
Like WongelTube on Facebook. Don’t Miss the new Mezmur.